በናይጀሪያ ከ 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ አጠቃላይ ፈተና መውሰድ ይጀምራሉ፡፡

በናይጂሪያ ከዛሬ ጀምሮ ከ1.5 ሚሊየን በላይ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ሀገር አቀፍ ፈተና መውሰድ እንደሚጀምሩ ተነግሯል፡፡

የኮሮና ቫይረስ መከሰቱን ተከትሎ ከመጋቢት ወር ጀምሮ ትምህርት የተቋረጠባቸው ተማሪዎች የማካካሻ ትምህርት ለሁለት ሳምንታት ሲወስዱና ለፈተና ሲዘጋጁ እንደነበሩ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የትምህርት ቤቶች ኃላፊዎች እንዳሉት ፈተናውን የሚወስዱት ተማሪዎች አካላዊ ርቀታቸውን ጠብቀው እንደሚቀመጡ ተናግረዋል፡፡

ፈተናውን የሚወስዱት ተማሪዎች በቀጣዩ አመት ወደ ዩኒቨርስቲ ለመግባት የሚያስችላቸውን ነጥብ ለማግኘት የሚያስችላቸው መሆኑ ተነግሯል፡፡

በናይጀሪያ 1.5 ሚሊየን የሚሆኑ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በ19 ሺህ ትምህርት ቤቶች ትምህርታቸውን እንደተከታተሉ ዘገባው ጠቁሟል፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
ነሀሴ 11 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *