በኦሮሚያ ክልል በዛሬው ዕለት የተጠራ አመጽ ቢኖርም በብዙ ከተሞች ሰላማዊ እንቅስቃሴ መኖሩን ነዋሪዎች ተናገሩ።

በኦሮሚያ ክልል በዛሬው ዕለት በድምጻዊ ሃጫሉ ግድያ ምክንያት የታሰሩ ፖለቲከኞች እና ዜጎች ይፈቱ በሚል የአመጽ እንቅስቃሴዎችን ለማካሄድ ጥሪ መደረጉ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እና በማህበራዊ ሚዲያዎች ጥሪ ተላልፎ ነበር።

ይሄንን የአመጽ ጥሪም የፌደራል ፖሊስን ጨምሮ የክልሉ መንግስት ህገወጥ ነው የዜጎችን የመስራት እና በሰላም የመንቀሳቀስ መብቶችን የሚገድብ በመሆኑ ሰዎች ከዚህ ህገወጥ ተግባር እንዲቆጠቡ ጥሪ አስተላልፎ ነበር።

ኢትዮ ኤፍ ኤም ወደ ኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የዛሬ ውሎ ምን ይመስላል ሲል ነዋሪዎችን ጠይቋል።

በተለይም በሐረር፣ ድሬዳዋ፣ አምቦ፣ ሻሸመኔ፣ አርሲ ነገሌ፣አዲስ አበባ ዙሪያ ሁሉም ከተሞች እና በሌሎችም የክልሉ ከተሞች የሚኖሩ ነዋሪዎች እንዳሉን ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንደቀጠለ መሆኑን ከነዋሪዎቹ ሰምተናል።

በከተሞቹ፣ካፌዎች እና ሱቆች ክፍት መሆናቸውን ጨምሮም የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንደከዚህ በፊቱ መኖሩን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ የአመጽ ጥሪ መኖሩን መስማታቸውን ተናግረው በከተሞቹ የጸጥታ አስከባሪዎች በብዛት በመኖራቸውን የተጠራው አመጽ አለመሳካቱን ነግረውናል።

የኦሮሚያ ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በበኩላቸው በክልሉ ለዛሬ በነዋሪዎች ላይ ጥቃት ለመፈጸም የተጠራው የጥፋት ጥሪ በክልሉ ነዋሪዎች ብልሃት እና በጸጥታ ሃይሉ ጥረት ከሽፏል ብለዋል።

አሁን ላይ የክልሉ እንቅስቃሴ ሰላማዊ መሆኑን አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ነግረውናል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ነሀሴ 12 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *