ናይጄሪያ የአየር ክልሏን ለዓለም አቀፍ በረራዎች ክፍት ልታደርግ መሆኑን አስታወቀች።

ናይጄሪያ በያዝነው ወር መጨረሻ ላይ አየር መንገዶቿን ለዓለም አቀፍ በረራዎች ክፍት እንደምታደርግ የሀገሪቱ አቪዬሽን ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

ሀገሪቱ ከአውሮፓውያኑ መጋቢት 23 ቀን ጀምሮ አየር መንገዶቿን በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት ዝግ አድርጋ ቆይታለች፡፡

የሀገሪቱ አቪዬሽን ሚኒስትር እንዳሉት በየቀኑ አራት በረራዎች ሌጎስ እና አቡጃ ላይ ያርፋሉ ፡፡

ከየትኛው ሀገር እንደሚመጡ ግን ሚኒስትሩ አልተናገሩም ፡፡

መደረግ ያለበትን ጥንቃቄ ሁሉ ካደረግን መንገደኞቻች በሰላምና ደህንነታቸው ተጠብቆ ይጓጓዛሉ ብለዋል፡፡

በናይጄሪያ ከሀምሌ ወር ጀምሮ የሀገር ውስጥ በረራዎች የሚደረጉ ሲሆን በዚህ ወቅት የተመዘገበ የኮሮና ቫይረስ ኬዝ አለመኖሩን ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡

ከአፍሪካ በህዝብ ብዛት ቁጥር አንደኛ የሆነቸው ናይጄሪያ ከ49 ሺ በላይ የኮሮና ቫይረስ ተያዦችን ሪፖርት አድረጋለች፡፡

በወረርሽኙ ምክንያትም 975 ሞት በሀገሪቱ ተመዝግቧል፡፡

በትግስት ዘላለም
ነሀሴ 12 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *