አዲስአበባ በመረጠችው ከንቲባ እንድትተዳደር ኢዜማ አሳሰበ።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ አዲስ አበባ አንድም በመረጠችው ከንቲባ ለመተዳደር አልቻለችም አሁን እየታዩ ያሉት የሹመት ሂደቶች ለውጥ የሚፈጥሩ አይደለምም ብሏል ዛሬ በሰጠው መግለጫ ።

የኢዜማ ምክትል መሪ አንዷለም አራጌ እንዳሉት የከንቲባ ሹመት ሂደቱ ጉልቻ ቢቀየር ወጥ አያጣፍጥ ነውና ትክክለኛ መፍትሄ መሆን ያለበት ህዝቡ በሚፈልገው መንገድ ከንቲባውን እንዲመርጥ ምርጫ ማካሄድ ብቻ ነው ብለዋል።

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የተራዘመው ሀገራዊ ምርጫም ቢሆን በቀጣይ ጊዜ ስለመካሄዱ የሚያመላክት ፍንጭ የለም የሚሉት ምክትል መሪው በሀገሪቱ ምርጫ የሌለ እስኪመስል ድረስ ለምርጫ የሚደረገው እንቅስቃሴ ሞቷልተ ብለዋል።

በመሆኑም ለቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ በቂ ዝግጅት ይደረግ ዘንድ ከወዲሁ እንቅስቃሴዎች ሊጀመሩ ይገባል ሲል ጠይቋል።

በትግስት ዘላለም
ነሀሴ 15 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *