የጃፓኑ ጠቅላይ ሚንስትር ሽንዞ አቤ በገጠማቸው የጤና እክል ሳቢያ በፍቃዳቸው ስልጣን ሊለቁ እንደሚችል እየተነገረ ነው፡፡

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚንስትር ሽንዞ አቤ በዛሬው እለት በድጋሜ ወደ አንድ የቶኪዮ ሆሰፒታል በአንቡላስ ተወስደው ሰባት ሰዓታትን የፈጀ ምርመራ አድርገዋል፡፡

አቤ የህክምና ውጤታቸው ከአንድ ሳምንት ቀደም ብሎ እንደሚደርሳቸው ሮይተርስ የሀገሪቱን መገናኛ ብዙሀን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚንስትር ካትሱኖቡ ካቶ እንዳሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ መደበኛ ምርመራዎች እንደተደረገላቸው ጠቅሰው የጤናቸው ጉዳይ ያን ያህል የሚያስጨንቅ አይደለም ብለዋል፡፡

ሽንዞ አቤ አቅም ካጠራቸውና በሽታቸውን መቋቋም ከተሳናቸው የሀገሪቱ የፋይናንስ ሚንስትርና ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ታሮ አሶ ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው እንደሚሾሙ ተገልጧል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሩ ስልጣን ለመልቀቅ መወሰናቸውን ከገለፁ እንኳን በመደበኛነት በምርጫ እስከሚተኩ ድረስ በስልጣን ላይ እንደሚቆዩም እየተነገረ ይገኛል፡፡

በሀገሪቱ ታሪክ ረጅም ዓመት ያስቆጠሩት እኚህ አቤ በአጎታቸው ልጅ ከተሾሙ በኋላ በርካታ አመታትን ስልጣን ላይ ቀይተዋል፡፡

ምናልባትም አሁን የሚለቁበት ጊዜ የተቃረበ ሳይሆን እንዳልቀረ በሰፊው እየተነገረ ነው፡፡

ዊክሊ መፅሔት ባሳለፍነው ሀምሌ 6 ቀን አቤ በቢሯቸው በስራ ላይ ሳሉ ድንገት ታመው ደም አስመልሷቸው ነበር ሲል በሰፊው መዘገቡ ይታወቃል፡፡

በደረሰ አማረ
ነሀሴ 18 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *