የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የኮሮና ቫይረስ መከላከያ እጥረት እንደገጠመው አስታወቀ።

በማረሚያ ቤቶች ውስጥ የሳኒታይዘር እና የአልኮል አቅርቦት እንደሌለ ነው የተገለጸው፡፡

የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ለታራሚዎች የንፅህና መጠበቂያ ሳሙና እና ሶፍቶችን ቢያቀርብም እንደ አልኮል እና ሳኒታይዘር የመሳሰሉ የንጽህና መጠበቂያዎች እንደሌሉ ነው ያስታወቀው፡፡

የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ሀላፊ አቶ ገረመው አያሌው ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ማረሚያ ቤቶቹ ለታራሚዎች የተለያዩ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን እያቀረቡ ቢሆንም በተወሰኑ ቁሳቁሶች ላይ ግን ከፍተኛ እጥረት አለ ብለዋል፡፡

እስካሁን ድረስ በፌደራል ደረጃ በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች ውስጥ አንድም ታራሚ በኮሮና እንዳልተያዘ የተናገሩት ሀላፊው አሁንም ከፍተኛ ጥንቃቄ እየተደረገ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በማረሚያ ቤት ለሚገኙ ሁሉም የህግ ታራሚዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ እንዲደርሳቸው ተደርጓል ብለዋል፡፡

በመሆኑም ሀገር በቀል ድርጅቶች እና ባለሀብቶች ለታራሚዎች የሚሆን የንጽህና መጠበቂያዎችን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ነሀሴ 18 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *