የሱዳን አማፅያን ለ17 ዓመታት የዘለቀውን ግጭት ለማስቆም ከመንግስት ጋር ተስማሙ፡፡

የሱዳን ዋና የአማፅያን ህብረቱ ከመንግስት ጋር ቁልፍ የሰላም ስምምነት ለማከናወን መስማማታቸውን ታዋቂው የዜና ወኪል ሱና ዘግቧል፡፡

የሀገሪቱ መንግስት ከአማፅያኑ ጋር የሰላም ስምምነቱ ታላሚ ያደረገው ለ 17 ዓመት የዘለቀውን ግጭት ለማስቆም መሆኑ ተገልጧል፡፡

የሱዳን አብዮታዊ ግንባር (SRF) ፤ የምዕራብ ዳርፉር ክልል አማፅያን እና በደቡብ ኮርዶፋን ክልል የትጥቅ ትግል የሚያደርጉ ሀይሎች ከመንግስት ጋር የሰላም ስምምነት ለማድረግ ፍቃደኛ መሆናቸው ዘገባው ጠቅሷል፡፡

እንደ አውሮፓውያኑ ከ2019 መገባደጃ ጀምሮ የእረጅም ጊዜ ውይይቶችን ሲያስተናግዱ ቆይተዋል፡፡ አሁን ግን አማፅያኑ ከመንግስት ጋር ወደ ወሳኝ ምዕራፍ ለመሸጋገር ቁልፍ የሰላም ስምምነት ለማድረግ መስማማታቸው ታውቋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሙሉቀን አሰፋ
ነሀሴ 25 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *