የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ለ61 ፖሊስ አባላት የማዕረግ እድገት ሰጠ።

በዚህም መሰረት 2 የምክትል ኮሚሽርነት 7 የረዳት ኮሚሽርነት እና ለ52ቱ ደግሞ ከኮማደር እስከ ኢንስፔክተርት ማዕረግ መስጠቱን አስታውቋል፡፡

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽር ጄኔራል ጀማል አባሶ እንደተናገሩት የዛሬው ሹመት በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በማዕረግ ደረጃም ሆነ በብዛት ከፍተኛው ነው፡፡

ከላይ እስከ ታች ያለው የተቋሙ አመራር እና ሰራተኛ ተናቦ በመስራቱ ባለፉት ሁለት ተከታታይ ዓመታት ኮሚሽኑ ውጤታማ መሆኑን አስታውሰው ይህም ለመንግስት የቀረቡ የሹመት ጥያቄዎች ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት እንዲኖራቸው አስችሏል ብለዋል ኮሚሽነሩ፡፡

ኮሚሽነር ጀማል አክለውም መስራት ለውጤትና ለሹመት ያበቃል ያሉት
ኮሚሽነር ጀነራሉ ለተሿሚዎች በሰጡት መመርያ እንዳሉት ዛሬ ያገኛችሁት ሹመት ለፖሊስ ከፍተኛው ሹመት ነው፡፡

የተሰጣችሁ ሹመት የበለጠ ኃላፊነትን እንድትሸከሙ የሚያደርግ እንጅ ከተልዕኮ የሚያዘናጋ ባለመሆኑ ለከፍተኛ መስዋዕትነት መዘጋጀት እለባችሁ ብለዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ነሀሴ 25 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *