ግብፅ በፀረ-ሽብር ዘመቻ 77 አክራሪ ታጣቂዎች መግደሏ አስታወቀች፡፡

ግብፅ በ30 ቀናት ውስጥ ባከናወነችው የፀረ-ሽብር ዘመቻ ከ70 በላይ ፅንፈኛ ታጣቂዎችን መገደላቸውን የሀገሪቱ ጦር ሀይል ተናግረዋል፡፡

በዘመቻው መሪዎቻቸውን ጨምሮ 73 አሸባሪዎች የተገደሉት በሰሜናዊ ሲናይ ይኖሩበታል ተብሎ ታላሚ በተደረገ መኖሪያ ቤቶች ላይ በተከናወነ ጥቃት መሆኑን ጦሩ ይፋ አድርጓል፡፡

ፅንፈኛ የግብፅ አክራሪ ታጣቂዎችን ለማፅዳት በተወሰደ እርምጃ 77ቱ መገደላቸውን ያሳወቀው የሀገሪቱ ጦር በጠቅላለው ከ317 በላይ ቤቶች እና ምሽጎች መደምሰሳቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕረስ ዘግቧል።

በዘመቻው እጅግ አደገኛ በሚል የሚታወቁ ሁለት ታጣቂ ግለሰቦችም ተገለዋል ተብሏል፡፡

እነዚህም በወቅቱ ካርታን ጨምሮ በርካታ የሽብር ጦር መሳሪያዎችን ታጥቀው እንደነበር ዘገባው ተመልክቷል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በደረሰ አማረ
ነሀሴ 25 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *