የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ሰራተኞች ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ17 ሚሊየን ብር በላይ የቦንድ ግዢ እንደሚፈጽሙ አስታወቁ፡፡

የኮሚሽኑ አመራርና ሠራተኞች ከ17 ሚሊዮን 327 ሺህ ብር በላይ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል ቦንድ ለመግዛት ወሳኔ አስተላልፈዋል፡፡

ሰራተኞቹ ከጥቅምት ወር 2013 ዓ..ም ጀምሮ ከደመወዛቸው በሚቆረጥ የአንድ ወር የተጠራ ደመወዛቸውን በ17 ሚሊዮን 327 ሺህ ብር ቦንድ ለመግዛት ነው ውሳኔ ያስተላለፉት፡፡

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽር ጄኔራል ጀማል አባሶ እንዳሉት የኢትዮጵያ መንግስት የመጀመሪያ የውሃ ሙሌትን በተሳካ ሁኔታ በማጠናቀቅ ታሪክ ሠርቷል፡፡

ይህ ስኬት ለአንድ አካል ተለይቶ የሚሰጥ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ስኬት ነው ብለዋል፡፡

እንደ ኮሚሽነር ጀኔራሉ ገለፃ ከህዳሴው ግድብ የውሃ ሙሊት ጋር ተያይዞ የግብጽ ኃያልነትን እያነሱ በሃገራችን ላይ አደጋ እንደሚደርስ በርካቶች ያሟርቱ እንደነበር አስታውሰው፤ መንግስት የታችኞች ተፋሰስ ሃገራትን በማይጎዳ መልኩ የውሃ ሙሊቱን ማጠናቀቁ በርካታ ሃገራትን እንዳስገረማቸው ተናግረዋል፡፡

የተቋሙ አመራሮችና ሠራተኞች የህይወት መስዋዕትነት ለመክፈ መዘጋጀታቸውን የገለጹት ኮሚሽነሩ ከህይወት መስዋዕትነት መለስ ግን የምንችለውን እናደርጋለን ብለዋል፡፡

የሁሉም ማዕከል ማረሚያ ቤት አስተዳዳሪዎች ለ5ኛ ጊዜ የ1 ወር ደመወዛቸው በአንድ ዓመት ተከፍሎ በሚያልቅ ቦንድ ለመግዛት መስማማታቸውን አረጋግጠዋል፡፡

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ከ5,700 በላይ ሚሊተሪ እና ሲቪል ሰራተኞች ያሉት ግዙፍ ተቋም ነው፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ነሀሴ 25 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *