ኦነግ ከፖርቲው ህግና ስርአት ባፈነገጠ መልኩ በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን አሳሳች መግለጫዎችን ሲሰጡ በነበሩ አመራሮቹ ላይ እርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ።

የኦነግ ቃላ አቀባይ አቶ ቀጀላ መርዳሳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የተወሰኑ ሰዎች በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን በመቅረብ አላስፈላጊ መግለጫዎችንና መልዕክት በማስተላለፋቸው ምክንያት በተፈጠረ ውዝግብ ላይ ብሔራዊ ምክር ቤቱ በጠቅላላ ጉባኤ በዲሲፕሊን እንዲጠየቁ የሚያስችል ውይይት ማድረጉን ተናግረዋል።

በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን በአመራሮች መካከል የርዕዮተ አለም ልዩነት እንዳለ የሚነገረው ትክክል አለመሆኑንም አቶ ቀጀላ ተናግረዋል፡፡

ይህ አይነት ነገር እንዲፈጠር ባደረጉት አመራሮች ላይ ግን የዲሲፕሊን እርምጃ እንደሚወሰድ ነግረውናል፡፡

ቀደም ብሎ የፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት መጋቢት ላይ ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ቀጣዩ ጉባኤ የፊታችን ታህሳስ 2013 ዓ.ም እንዲካሄድ በመወሰኑ ይህም ጉዳይ በዚህ በጠቅላላ ጉባኤው ላይ ቀርቦ እንደሚታይ ነግረውናል፡፡

ከዚያ በፊት ግን ብሔራዊ ምክር ቤቱ ተሰብስቦ አሁን የተፈጠሩትን ጉዳዩች በመመልከት ውሳኔ ከሰጠ በኃላ ለጠቅላላ ጉባኤው ያቀርባል ብለዋል፡፡

የዲሲፕሊን እርምጃው የሚወሰድባቸው አመራሮች እነማን ናቸው? በሚል ላነሳንላቸው ጥያቄ ዝርዝር ጉዳዮች በውስጥ ጉዳይ የተያዙ በመሆናቸው መናገር አልችልም ብለውናል።

ኦነግ በአመራሮቹ መካከል የተነሳውን ውዝግብ ለመፍታት ያለመ ውይይት ታዛቢዎች ባሉበት ማካሄዱ ይታወሳል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ነሀሴ 28 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *