ቻይና በሆንግ ኮንግ ላይ ያወጣችዉ አዲስ የደህንነት ህግ የከተማዋን ነጻነት የሚነፍግ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገለጸ፡፡

የድርጅቱ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ተመራማሪ እንዳሉት ካሳለፍነዉ ሰኔ ወር ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገዉ አዲስ የደህንነት ህግ አሳሪና ነጻነትን በእጅጉ የሚገድብ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ተመራማሪዉ እንደሚሉት ይህ ህግ ዓለም አቀፍ ህጎችን ሳይቀር የሚጥስ ነው ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

በሆንግ ኮንግ ተደጋጋሚ የተቃዉሞ እንቅስቃሴዎች መደረጋቸዉን ተከትሎ ወጥቶ የተተገበረዉ ይህ ህግ የማህበረሰብ አንቂዎችና የገዝዉን ፓርቲ የሚቃወሙ አካላትን ለቃቅሞ ወደ እስር ቤት ለማስገባት በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀ መሆኑን ነዉ ተመራማሪዉ የተናገሩት፡፡

በዚሁ በአዲሱ ህግ 10 ሰዎች እስከሳሁ ለእስር የተዳረጉ ሲሆን ከነዚህ መካከልም የሚዲያ ባለቤቶችና የማህበረሰብ አንቂዎች ይገኙበታል፡፡

ይህን ሰበብ በማድረግም አሜሪካ ቻይነቃ በሆንግ ኮንግ ላይ እያሳደረች ያለዉን ጫናና የሰብአዊ መብት ጥሰት ዓመላቀፋ ማህበረሰብ እንዲያወግዝ ግፊት እየፈጠረች ትገኛለች፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሙሉቀን አሰፋ
ነሀሴ 29 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *