በአዲስ አበባ ማስክ ሳያደርግ ወደ ታክሲ ውስጥ የገባ ተሳፋሪ 500 ብር እንደሚቀጣ ያውቃሉ?

ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ መከሰትን ተከትሎ በወጣው የትራንስፖርት አገልግሎት መመሪያ ላይ ተሳፋሪዎች ማስክ ሳያደርጉ ትራንሰፖርት መጠቀም እንደማይችሉ ቢከለክልም ባላደረጉት ላይ ያስቀመጠው የቅጣት መጠን አለመኖሩ ይታወሳል፡፡

በመመሪያው ላይ ዛሬ በተደረገው ማሻሻያም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ወይም ማስክ በማያደርጉ ተሳፋሪዎች ላይ የ500 ብር ቅጣት መጣሉን የቢሮው የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሀላፊ አቶ አረጋዊ ማሩ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ማስክ ያላደረጉ ተሳፋሪዎችን የጫነ አሽከርካሪና ረዳት ላይም እያንዳንዳቸው 1 ሺ ብር እንዲቀጡ መወሰኑን አቶ አረጋዊ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የተጣለው የምሽት 2 ዓት ሰዓት ገደብ ከተነሳ የቆየ ቢሆንም አሁንም ተሳፋሪዎች እንዲሁም አሽርካሪዎች ላይ ብዥታ መፈጠሩን ኢትዮ ኤፍ ኤም ታዝቧል፡፡

ይህንንም ተከትሎ ትራንስፖርት ሰጪዎች ላይ ተጥሎ የነበረው የሰዓት ገደብ ከተነሳ መቆየቱን እና ይህ ብዥታ ሊኖር እንደማይገባ ቢሮው ለጣቢያችን አክለው ተናግረዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በትግስት ዘላለም
ጷግሜ 2 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *