መንግሥት በንፁሃን ዜጎች ላይ የተፈፀመውን አሰቃቂ ወንጀል የሚዘክር ቋሚ መታሰቢያ እንዲያቆም አብን ጠየቀ።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል።

ንቅናቄው በመግለጫው እንዳስታወቀው የአገሪቱ የዲሞክራሲ እና የፖለቲካ እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ መምጣቱንም አስታውቋል።

በአጠቃላይ አብን በጥናቴ አረጋግጫቸዋለሁ መንግስትም በቀጣይ የማስተካከያ እርምጃዎችን ሊወስድባቸው ይገባል ያላቸውን ጉዳዮች በዝርዝር አስቀምጧል።

በኦሮሚያ ክልል የተደረገው የዘር ማጥፋት ተገቢውን ትኩረት ያለማግኘቱና ችግሩን በአጭር ጊዜም ይሁን በዘለቄታ ለመፍታት የሚታየው ዳተኝነት ፓርቲውን ክፉኛ እንደሚያሳስበውም ገልጿል። በመሆኑም

ሀ) የተፈፀመው ወንጀል የዘር ማጥፋት መሆኑ ታምኖበት በስሙ እንዲጠራና ለተፈፀመው ወንጀልም ይፋዊ ይቅርታ እንዲጠየቅ፤

ለ) መንግሥት የተፈፀመውን የዘር ፍጅት የሚያጣራና የሚመረምር ልዩ የምርመራ ኮሚሽንና አቃቤ ሕግ ጽ/ቤት እንዲያቋቁምና ወንጀለኞች የሚዳኙበት ልዩ ችሎት እንዲሰይም፤

ሐ) መንግሥት በንፁሃን ዜጎች ላይ የተፈፀመውን አሰቃቂ ወንጀል የሚዘክር ቋሚ መታሰቢያ እንዲያቆም፤

መ) ችግሩን በዘለቄታ ለመፍታት በክልሉ በሚኖሩ የተለያዩ ማህበረሰቦችና ህዝቦች መካከል የእርቅና የመግባባት ስራዎች እንዲጀመሩ እንዲሁም የኦሮሚያ ክልልም በክልሉ ለሚኖሩ ኦሮሞ ያልሆኑ ማህበረሰቦችና ህዝቦች ሰብአዊና ህገ መንግሥታዊ መብቶቻቸው የሚከበሩበት ዋስትና እንዲሰጥ ንቅናቄው ጠይቋል።

በሳሙኤል አባተ
ጷግሜ 2 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *