በግብፅ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከአንድ መቶ ሺህ ተሻገረ፡፡

በግብፅ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 100 ሺ 41 የደረሰ ሲሆን ይህ የተጠቂዎች ቁጥርም ከአፍሪካ ሀገራት ከደቡብ አፍሪካ በመቀጠል ሁለተኛው ከፍተኛ ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በግብፅ 5ሺ 541 ሰዎችም በቫይረሱ ምክያት ህይወታቸውን ማጣታቸውንም የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ማስታወቁን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

ከአፍሪካ ከፍተኛውን የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ያስመዘገበችው ሀገር ደቡብ አፍሪካ 639 ሺ 362 ዜጎቿ በኮሮና ቫይረስ ሲያዙባት ከ15 ሺ በላይ ሰዎችም ህይወታቸው አልፏል፡፡

በ3ተኝነት ደረጃ ላይ ደግሞ 73 ሺ 780 ተጠቂዎችን በማስመዝግብ ሞሮኮ ተቀምጣለች፡፡

ኢትዮጲያም ቢሆን 59 ሺ 648 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ የተያዙባት 4ተኛዋ ሀገር መሆኗንም መረጃው ያሳያል፡፡

በሔኖክ አስራት
ጷግሜ 3 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *