ኢትዮጵያዊያን በነሀሴ ወር ብቻ ከ152 ሚሊዮን በላይ ብር ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፍ ማድረጋቸው ተገለጸ።

የህዳሴው ግድብ ግንብታ ብሔራዊ የሕብረተሰብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሀይሉ አብርሃም ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት በነሀሴ ወር ብቻ ኢትዮጵያዊያን በቦንድ፣በአጭር የጽሁፍ መልዕክት እና በሌሎች የድጋፍ መንገዶች በነሀሴ ወር 152 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገዋል።

በ2012 በጀት ዓመት እስከ ሰኔ 30/2012 ዓ/ም ጠቅላላ የተሰበሰበው 745 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ሲሆን ይሆን በዓመቱ ትልቁ ሰኔ ላይ የተሰበሰበው 87 ነጥብ 25 ሚሊዮን ብር ነበር።

ግድቡ ሐምሌ ወር ላይ ውሃ መያዙን ተከትሎም ለግድቡ የተደረገው ድጋፍ የጨመረ ሲሆን 119 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር ተሰብስቧል።

አቶ ሃይሉ ኢትዮጵያዊያን አዲሱ ዓመት ለግድቡ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

በ84 ቢሊዮን ብር ከ10 ዓመት በፊት በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ የተጀመረው ታላቁ የህዳሴ ግድብ 78 በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን ከ120 ቢሊዮን በላይ ብር ወጪ ተደርጓል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሳሙኤል አባተ
ጷግሜ 3 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *