በኢትዮጵያ በ2013 በጀት ዓመት በየወሩ 470 ሺህ ሰዎችን የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ለማድረግ መታቀዱን የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

ኢንስቲትዩቱ ዛሬ በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው በቀጣዩ ዓመት በየወሩ በአማካኝ 470 ሺህ ሰዎችን የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ለማድረግ እቅድ ተይዟል።

እስካሁን በተደረገው የግንዛቤ ፈጠራ ስራ 40 ሚሊዮን ህዝብ ስለ ኮሮና ቫይረስ ምንነት፣መተላለፊያ መንገዶች እና መደረግ ስላለባቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች ትምህር መሰጠቱ ተገልጿል።

ቫይረሱ ወደ ኢትዮጵያ ከገባበት ጊዜ አንስቶም 1 ቢሊዮን የሚደርሱ የሕክምና ቁሳቁሶች ለክልሎች መሰራጨታቸውም በመግለጫው ላይ ተገልጿል።

ሕብረተሰቡ፣አምራቾች እና የተለያዩ ተቋማት ከ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን በላይ ብር ድጋፍ አድርገው ይሄው ድጋፍ ለሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳድሮች መሰራጨቱ ተጠቁሟል።

በተጨማሪም 217 ሚሊዮን የላብራቶሪ ግብዓት እና ከ19 ሚሊዮን በላይ ልዩ ልዩ መድሃኒቶች ለሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳድሮች መሰራጨታቸውን ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጷግሜ 4 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *