የዓለም ባንክ እና የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል በ 5 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በኢትዮጵያ ዘመናዊ የምርምር ማዕከል ሊገነቡ ነው።

የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለምስራቅ አፍሪካ አገራት አገልግሎት የሚሰጥ ቤተ ሙከራ ማዕከል በ5 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ወጪ ሊገነባ መሆኑን አስታውቋል።

የቤተ ሙከራ ማዕከሉ ለመገንባት የሚያስፈልገውን ወጪ የዓለም ባንክ እና የአፍሪካ በሽታዎች መቆጣጠሪያ ማዕከል ይሸፍናሉ የተባለ ሲሆን ማዕከሉ በተለያዩ የጸረ ተዋህሲያን የምርምር ስራዎችን እና ሌሎች ከጤና ጋር የተያያዙ የምርምር ስራዎችን ለማካሄድ ያግዛል ተብሏል።

የምርምር ማዕከሉ በ2013 በጀት ዓመት እንደሚጀመርም ኢንስቲትዩቱ ገልጿል።

የምርምር ማዕከሉ በአዲስ አበባ ይገነባል የተባለ ሲሆን በሁሉም ክልሎች ደግሞ 15 የምርምር ማዕከላትን እንደሚገነቡም የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዛሬ ረፋድ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጷግሜ 4 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *