የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለ508 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገ።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የ2013 አዲሱን ዓመት ምክንያት በማረግ ለ508 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ መደረጉን የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡

በክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕግ አገልግሎት ዘርፍ ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ንጋቱ ዓለሙ በሰጡት መግለጫ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚገኙ ሶስቱም ማረሚያ ቤቶች ለሚገኙ 508 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

በክልሉ ይቅርታ ከተደረገላቸው ውስጥ 501 ወንዶች ሲሆነ፣ 7ቱ ሴቶች መሆናቸውን ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ተናግረዋል፡፡

የይቀርታው ተጠቃሚ የሆኑት የሕግ ታራሚዎች፣ በማረሚያ ቤት ቆይታቸው በፈጸሙት ወንጀል የተጸጸቱና ተገቢውን ትምህርት የወሰዱ ናቸው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ንጋቱ፣ የይቅርታ መስፈርቱን ማሟላታቸው በቦርዱ የተረጋገጠላቸው መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡

በይቅርታው የተካከቱት ታራሚዎች በማረሚያ ቤት ውስጥ ከ1 ዓመት ከ4 ወር አስከ 17 ዓመት ከ4 ወር ቆይታ የነበራቸው ናቸው ብለዋል፡፡

በዓሉን ምክንያት በማድረግ ይቅርታ የተደረገላቸው 312 ከመተከል ዞን ማረሚያ ቤት፣ 69 ከካማሺ ማረሚያ ቤት እና 127ቱ ደግሞ ከአሶሳ ዞን ማረቢያ ቤት መሆናቸውንም ነው የገለጹት፡፡

አዲሱን ዓመት በይቅርታና በይቅር ባይነት መጀመር ይገባል ያሉ ሲሆን ሀገራችን በለውጥ ሂደት ውስጥ በመሆኗ ይቅርታን ባህል ማድረግ ከሁሉም ይጠበቃል ብለዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ንጋቱ ዓለሙ፣ በማረሚያ ቤት የነበራቸውን ቆይታ እንደትልቅ ትምህርት በመውሰድ ወደ ህብረተሰቡ ሲቀላቀሉ ራሳቸውንና ሀገራቸውን የሚጠቅም ሥራ እንዲሠሩም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የሕግ ታራሚዎቹ ከነገ ጀምሮ ወደ ህብረተሰቡ እንደሚቀላቀሉም ተገልጿል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ጷግሜ 5 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *