የቀድሞው የማሊ ፕሬዚዳንት ሙሳ ትራኦሪ አረፉ

የቀድሞው የማሊ ፕሬዝዳንት ሙሳ ትራኦሬ በዋና ከተማዋ ባማኮ ባለው ቤታቸው ነው ያረፉት፡፡

ትራኦሪ እድሜቸው  83 ነበር ፡፡

ትራኦሪ በ 1968 በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን የያዙ ሲሆን እ.አ.አ. በ 1991 በተራቸው  በወታደሮች እስኪወገዱ ድረስ ፕሬዝዳንት ሆነው አገልግለዋል ፡፡

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ወጣት የማሊ ፖለቲከኞችን በማማከር የሀገር ሽማግሌነትን ሚና ተጫውተዋል ፡፡

ሞታቸው  ከነፃነት በኋላ ከማሊ አራተኛ መፈንቅለ መንግስት ጋር ይገጥማል ፡፡

ከአንድ ወር በፊት በሀገሪቱ መፈንቅለ መንግስት መደረጎ የሚታወስ ነው እንደ ቢቢሲ አፍሪቃ ዘገባ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
መስከረም 6 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *