በኡጋንዳ ከ200 በላይ ታራሚዎች ከእስር ቤት አመለጡ።

ከ 200 በላይ ታራሚዎች በሰሜን ምስራቅ ከሚገኝ እስር ቤት ማምለጣቸው ተሰምቷል፡፡ የጸጥታ ሀይሎች የህዝቡን ትብብር እየጠየቁና እያሰሱ ናቸው፡፡

ሞሮቶ ከተሰኘው ማረሚያ ቤት ሲያመልጡ እስረኞቹ ወታደር ገድለዋል ተብሏል፡፡

ጦር ሀይሉና የእስር ቤቱ ጥበቃዎች 15 ሽጉጦችና በርካታ ጥይቶች ይዘው የተሰወሩትን እስረኞች እያሰሱ ናቸው፡፡

የጦር ሀይሉ ቃል አቀባይ እንደተናገሩት 2 እስረኞች ተገድለዋል 2 ሌላ እስረኞች ደግሞ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ማረሚያ ቤቱ ከ ሞሮቶ ተራራ ስር የተገነባ ነው፡፡

እንደ አሶሴትድ ፕሬስ ዘገባ ከሆነ እስረኞቹ በቀላሉ እናዳይለዩ ቢጫ ዩኒፎርማቸውን በማውለቅ ነው ወደ ተራራው መውጣት የጀመሩት፡፡

የተኩስ ልውውጡ በሞሮቶ አከባቢ ያለ የንግድም ሆነ ማንኛውንም መደበኛም እንቅስቃሴ አስቁሟል፡፡

ሞሮቶ በከብት ዝርፍያና በጦር መሳርያ ጥቃት የምትተወቀው ካራሞጃ ውስጥ የምትገኝ ትልቅ ከተማ ነች፡፡

በሔኖክ አስራት
መስከረም 7 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *