ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መሰብሰቢያ አደራሽ እያካሄደ ይገኛል፡፡

የዛሬው የምክር ቤቱ አጀንዳዎች

1. የም/ቤቱን 5ኛ አመት የስራ ዘመን 3ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ ማጽደቅ፣

2. የሚኒስትሮችን ሹመት መርምሮ ማጽደቅ፣

3. የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት እጩ ዳኞች ሹመት መርምሮ ማጽደቅ

4. የሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉደዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የህግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የጤና ሚኒስቴር አገራዊ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምላሽ ቀጣይ እርምጃዎችን በተመለከተ ባቀረበው ሪፖርትና ክምረ ሀሳብ ላይ ያቀረቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ማጽደቅ፣

5. በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በኮሪያ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ መካከል ለኮሮና ቫይረስ(COVID-19) አስቸኳይ ጊዜ ምላሽ የበጀት ድጋፍ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ማጽደቅ፣

6. በኢትዮጵያ ፈዴራላዊ ዲሞክራሳዊ ሪፓብሊክ እና በኮሪያ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ መካከል ለኮሮና ቫይረስ(COVID-19) የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች አቅርቦት ለማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ማጽደቅ፣

7. በኢትዮጵያ ፈዴራላዊ ዲሞክራሳዊ ሪፓብሊክ እና በዳንስኬ ባንክ ኤ.ስ መካከል ለአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ማጽደቅ፣ መሆኑን ምክርቤቱ ገልጿል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

መስከረም 12 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *