አሜሪካ እስከ መጭው ታህሳስ ድረስ 378 ሺህ ዜጎቿን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በሞት እንደምታጣ ተገለጸ።

በዓለማችን በኮሮና ቫይረስ ከሚሞቱ አምስት ሰዎች መካከል አንዱ አሜሪካዊ ነውም ተብሏል።

በአሜሪካ በኮቪድ 19 የሞተው ሰው ቁጥር ወደ 200 ሺህ እየተጠጋ ነው።

ይህ አሀዝ በአለም አቀፍ ደረጃ ከሚሞተው አምስቱ አንዱ በአሜሪካ ይገኛል እንደማለት ነው፡፡

እንደ ጤና ባለሙያዎች ትንበያ ከሆነ በአሜሪካ በኮቪድ 19 የሟቾች ቁጥር 2020 መጨረሻ ላይ 378 ሺህ ይደርሳል፡፡

ትናንት በአሜሪካ በኮሮና ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ወደ 200 ሺህ እንደተጠጋ አልጀዚራ በዘገባው ያስነበበ ሲሆን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወረርሽኙን የያዙበት መንገድ ለሁለተኛ ዙር ለሚያደርጉትን ከባድ የምርጫ ፉክክር ነጥብ የሚጥሉበት ዋነኛ ጉዳይ ይሆናል እየተባለ ነው፡፡

እንደ ጆን ሆፕኪንስ ሪፖርት ከሆነ በ 24 ሰአታት በተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር 199 ሺህ 818 ደርሷል፡፡

በአሜሪካ በኮሮና የተጠቃው ቁጥር በአለም ከፍተኛው ሲሆን ከ 6.8 ሚሊዮን ተሻግሯል፡፡

እንደ አሜሪካ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል ከሆነ ከሟቾች 70 በመቶ የሚሆኑት ዕድሜያቸው ከ 65 በላይ ናቸው፡፡

እንደ ሪዮተርስ ትንተና ከሆነ ደግሞ የየሳምቱ አማካይ ሞት ሲታይ አሜሪካ በየቀኑ 800 ሰዎችን በኮሮና ምክንያት እያጣች ነው፡፡

የሟቾች ቁጥር ለ አራት ሳምንታት መቀነስ ካሳየ በኋላ ባለፈው ሳምንት በአምስት በመቶ ጨምሯል፡፡

የዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የጤና ተቋም በ 2020 መጨረሻ የሟቸች ቁጥር 378 ሺህ የሚደርስ ሲሆን በታህሳስ በቀን 3 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ይሞታሉ ሲል አስደንጋጭ ትንበያውን አስቀምጧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በትግስት ዘላለም
መስከረም 12 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *