የማሊ የቀድሞ መከላከያ ሚኒስትር ጊዜያዊ የሀገሪቱ መሪ ሆነዋል።

የማሊ ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ እንዳሳወቀው የማሊ የቀድሞ መከላከያ ሚኒስትር ባህ ንዳው የሀገሪቱ ጊዜያዊ መሪ ተደርገው ሲሾሙ የመፈንቅለ መንግስቱ መሪ ኮሎኔል አሲሚ ጎይታ ደግሞ ምክትላቸው ሆነዋለል፡፡

በመፈንቅለ መንግስት ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ባቡር ኪዬታን አስወግዶ ወደ ስልጣን የመጣው ይህ ወታደራዊ መንግስት ከምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ስልጣኑን ለህዝብ አስረክቦ ወደ ወታደር ቤት እንዲመለስ ከፍተኛ ጫና ሲደረግበት ነው የከረመው፡፡

አሁን በጊዜያዊነት ሀገሪቱን እንዲመሩ የተሾሙት ንዳው ጡረታ የወጡ የፕሬዝዳንት ክዬታ ዋና ኮሎኔል ነበሩ፡፡

የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ባለፈው ሳምንት ምርጫ እስኪደረግ ለ 18 ወራት በሚቆይ የሽሽግግር ጊዜ ወታደር ያልሆነ ሲቪል ጊዜያዊ መሪ እንዲሾም አቋም ይዘው የነበረ ሲሆን በዚህ የሽግግር ጊዜ እንደ ምክትል መሪ ሆኖ ወታደር ቢሾም ሊቀበሉ እንደሚችሉ አሳውቀው ነበር፡፡

ንዳው በምዕራብ አፍሪካ ሀገራት (Ecowas) ወይንም በተቃዋሚ ፓርቲዎች ቅቡልነት ያገኙ ይሆን ወይ የሚለው ገና ግልፅ አለመሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ አስራት
መስከረም 12 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *