የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ክልላዊ እና ሀገራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ለመወሰን ውይይት እየተካሄደ ነው።

የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች እና የክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች መደበኛ ትምህርት የሚጀመርበትንና የ8ኛና 12ኛ ክፍል ክልላዊ እና ሀገራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ላይ ውሳኔ ለማሳለፍ በአዲስ አበባ ውይይት እያካሄዱ ነው።

እንዲሁም በግል ትምህርት ቤቶች ላይ እየቀረቡ ባሉ ቅሬታዎች ላይ እንዲሁም አዲሱ የትምህርት ስርዓት ዝግጅት አካሄድ እና ሁኔታ በውይይቱ ላይ የሚገመገም እና ውሳኔ የሚሰጠው ይሆናል ተብሏል።

የጎልማሶች ትምህርት አሰጣጥ ና አፈፃፀምም በውይይቱ ውሳሄ ከሚያገኙ ጉዳዬች መካከል ሲሆን በውይይቱ ላይ የተደረሰው ውሳኔም በነገው እለት ለህዝብ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።

በትግስት ዘላለም
መስከረም 12 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *