የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመቀነስ በሚል ለ6ወራት ዝግ ሆነው የቆዩት መጠጥ ቤቶች ከዛሬ ጀምሮ ክፍት እንደሚሆኑ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬኒያታ አስታውቀዋል፡፡
መጠጥ ቤቶቹ ከምሽቱ 4 ሰዓት በኋላ ዝግ እንዲሆኑና ፈፅሞ አገልግሎት መስጠት እንዳይችሉ ግን የሰዓት ገደብ ተጥሎባቸዋል ነው የተባለው፡፡
በሀገሪቱ በከሮና ቫይረስ ምክንያ የተጣሉ አንዳንድ እገዳዎች ለተጨማሪ 60 ቀናት እንዲራዘሙ የተደረገ ሲሆን የተጠበቀው የትምህርት ቤት ይከፈታል ዜና ሳይሰማ ቀርቷል፡፡
የሀገሪቱ ትምህርት ሚኒስቴር መምህራን ሪፖርት እንዲያደርጉ የጠየቀ ቢሆንም ፕሬዝዳንቱ ግን የትምህርት ተቋማትን የምንከፍተው የተማሪዎችን ደህንነት ማረጋገጥ የሚያስችል አቋም ላይ ስንሆን ብቻ ነው ብለዋል፡፡
ሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል እያደረገች ያለችውን ጥረት እና የተወሰዱ እርምጃዎችን በሚመለከት ፕሬዝዳንቱ ማብራሪያም ሰጥተዋል፡፡
ከ38 ሺ በላይ የከሮና ቫይረስ ተጠቂን ያስመዘገበችው ኬኒያ ከ700 በላይ ሞትም ተመዝግቦባታል፡፡
በሀገሪቱ ያለው የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ እየቀነሰ መምጣቱንና በትላንታናው እለት 53 ሰዎች ላይ ብቻ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን በሀገሪቱ የሚደረገው የላብራቶሪ ምርመራ እየቀነሰ መምጣቱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8
በትግስት ዘላለም
መስከረም 19 ቀን 2013 ዓ.ም











