የፌደራል ፖሊስ ነገ ለሚያደርገው የሰልፍ ትርኢት የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ::

የተሰጠው መግለጫ ይህ ነው።

መስከረም 20 ቀን 2013 ዓ/ም ከጠዋቱ 1፡30 እስከ 6፡30 ሰዓት በመስቀል አደባባይ የመንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የሰልፍ ትርኢት ይካሄዳል፡፡በዚህመሰረት፡-
 ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ኦሎምፒያ አደባባይ
 ከመገናኛ፣በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኒያለም፣በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያ አካባቢ
 ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻ ወልዴ ችሎት ወይም ፓርላማ መብራት
 ከቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ አገር አስተዳደር መብራት ወይም ኢሚግሬሽን መ/ቤት አካባቢ
 ከተክለሀይማኖት በሜትሮሎጂ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ
 ከተክለሀይማኖት፣በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣ኢሚግሬሽን ጥቁር አንበሳ የኋላ በር
 ከጌጃ ሰፈር፣ጤና ጥበቃ፣ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ
 ከሳሪስ በጎተራ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር አካባቢ
 ከጦር ኃይሎች፣ልደታ፣ፖሊስ ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ
 ከጦር ኃይሎች፣ልደታ፣ፖሊስ ሆስፒታል፣ሜክሲኮ፣ለገሀር መብራት የሚወስደው ለገሃር መብራት
የይለ ፍፈቃድ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ መሆኑን አሽከርካሪዎች ተገንዝበው የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *