ከአፍሪካ በስውር ወደ ሌሎች የዓለማችን አገራት የሚወጣው አመታዊ ገንዘብ ከ50 ቢሊዮን ወደ 89 ቢሊየን ዶላር ከፍ ማለቱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡

አህጉሪቷ በዋናነት ገንዘቡን የምታጣው በሙስና በታክስ ማጭበርበር እና በስርቆት እንደሆነ ነው የድርጅቱ ሪፖርት ያመላከተው፡፡

አፍሪካ ይህንን መጠን ያለው ገንዘብ የምታጣው ከሌሎች ሀገራት ጋር በምታደርገው የንግድ ልውውጥ ነው፡፡

ድርጅቱ ከአምስት አመታት በፊት በአዲስ አበባ በተደረገው ስብሰባ ላይ በተመሳሳይ መልኩ 50 ቢሊየን ዶላር በስወራ ታጣ እንደነበረ አስታውቆ ነበር፡፡

በመሆኑም በየአመቱ ከፍተኛ ገንዘብ በስወራ መልኩ እንደምታጣ ነው ሪፖርቱ የሚያሳየው፡፡

እንዲህ አይነት ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርና ሙስና የአፍሪካ ልማት እክል እየሆነ እንደሚገኝ ነው የተገለጸው፡፡

ህገወጥ የገንዘብ ዝውውሩ በከፍተኛ ሁኔታ አህጉሪቷ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንዲያጋጥማት ምክንያት መሆኑንም ነው በሪፖርቱ የተገለጸው፡፡

በአጠቃላይ የሀገራት ምጣኔ ኃብቱ እንዲጎዳና ድህነትና የኢኮኖሚ አለመጣጠን እንዲኖር ምክንያት ሆኗል ሲል በሪፖርቱ ላይ ማተቱን አልጀዚራ ዘግቧል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
መስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *