የኢሬቻ በዓል ሲከበር ከኮሮና ቫይረስ በመጠንቀቅ መሆን እንዳለበት የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳሰበ።

ኢንስቲትዩቱ የ2013 ዓ.ም የኢሬቻ በአልን አስመልክቶ ባወጣው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱ ላይ እንዳስታወቀው በዓሉ ሲከበር የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶችን በመተግበር ሊሆን ይገባል ብሏል።

በኢሬቻ የበአል አከባበር ስነ-ስርዓት ጊዜ ሁሉም ለኮቪድ 19 አጋላጭ ከሆኑ ለበአሉ ላይ መሰባሰብ፣ እርቀትን አለመጠበቅ፣ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ በአግባቡ አለመጠቀም፣ እጅን በሳሙናና በውሃ አለመታጠብ ወይም ሳኒታይዘር አለመጠቀም የመሳሰሉ የበሽታውን ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ ስለሚያባብሱ ሁሉም ማህበረሰብ ከወዲሁ ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል ሲልም አሳስቧል፡፡

ስለሆነም መሰባሰብን በማስቀረት፣ ርቀትን በመጠበቅና የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛን በአግባቡ መጠቀም እንደሚያስፈልግ አስጠንቅቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያውያን
መስከረም 21 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *