በ4 ክልሎች እና በ2ቱ ከተማ መስተዳደሮች ከመስከረም 27 እስከ መስከረም 30 ቀን 2013 ዓ.ም የፖሊዮ ክትባት እንደሚስጥ ፣ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል።
የፖሊዮ ቫይረሱ ከኢትዮጵያ ጠፍቶ የነበረ ቢሆንም ከጎረቤት ሀገራት በመጣ ቫይረስ ማገርሸቱ ተነግሯል ።
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ እንዳሉት ሁለቱን ከተማ መስተዳደሮች ጨምሮ በሱማሌ ፣ በኦሮሚያ ፣በደቡብ እና በሀረር ክልል የፖሊዮ ክትባቱ ይሰጣል ብለዋል ።
ክትባቱ ቤት ለቤት የሚካሄድ ሲሆን ከ5 አመት በታች የሆኑ 7 ሚሊየን ሕጻናት ይከተባሉ ተብሏል ።
ከዚህ በፊት የተከተቡ ህጻናትም ቢሆኑ በዘመቻው ይከተባሉ ተብሏል ።
የቢጫ ወባ ክትባትም በደቡብ እና በኦሮሚያ ክልሎች ከጥቅምት 13 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ አቶ አስቻለው ተናግረዋል ።
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8
በዳንኤል መላኩ
መስከረም 22 ቀን 2013 ዓ.ም