ለህግ የበላይነት መረጋገጥ ተግዳሮት የሆኑ ኢ መደበኛ አደረጃጀትም ይሁን ሸማቂ ሃይል ትጥቅ ይዞ እንዳይንቀሳቀስ ለማድረግ ከፍተኛ ስራ ይሰራል አሉ ፕሬዝደንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ፡፡

የዜጎች ደህንነት በምንም መልኩ አደጋ ላይ የሟይወድቁባት ሀገር ለመገንባት እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡

ዛሬ 5ኛ ዙር 6ኛ ዓመት የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ም/ቤቶች የጋራ መክፈቻ ሥነ ስርዓት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በመካሔድ ላይ ነው፡፡

ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ  የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡

ሰላም የሁሉም መሰረት ነው ያሉት ፕሬዝዳንቷ ህዝባችን በሰላም ወጥቶ እንዲገባ ፤ ሰርቶ ራሱንም ሆነ ሃገሩን እዲጠቅም ሰላም ወሳኝ ነው፡፡

ያሉ ሲሆን በአዲሱ ዓመትም የአገሪቱን ሰላም አስተማማኝ ደረጃ ላይ ለማድረስ የህዝቡ የነቃ ተሳትፎ ወሳኘ መሆኑን ገለጸዋል፡፡

ለህግ የበላይነት መረጋገጥ ተግዳሮት የሆኑ አደረጃጀቶች እና የታጠቁ ሃይሎች በመላ ሃገራችን ምንምዓይነት ህገ ወጥ ተግባራት እንዳይሰማሩ ለማድረግ እና ከመንግስት ውጪ ማንኛውም ኢ መደበኛ አደረጃጀትም ይሁን ሸማቂ ሃይል ትጥቅ ይዞ እዳይነቀሳቀስ ለማድረግ ከፍተኛ ስራ ይሰራል ብለዋል በንግግራቸው፡፡

የዜጎች ደህንነት በምንም ሁኔታ ውስጥ አደጋ ላይ የማይወድቅባት ሃገር ለመፍጠር እና የህግ የበላይነት የሚታይ እና የሚጨበጥበት ደረጃ ላይ ለማድረስ ትኩረት እደሚሰጥ አብራርተዋል፡፡

ዜጎች በደህንነት ስሜታቸው እንዲጎለብት ለማድረግ ይሰራል ብለዋል፡፡

ይህግ የበላይነትን ለማረጋገጥና ለማስከበር ተቋማትን የማደራጀት እና የማብቃት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡

የዳኝነት ስርዓታችን  እና ሁሉም የህግ አስከባራ ተቋሞቻችን ይበልጥ አሰራራቸውን እንዲያሻሽሉ በማድረግ በህግ የተሰጣቸውን ተልዕኮ መፈጸም የሚያስችላለቸውን አቅም እንዲገነቡ ይደረጋል፡፡

በተጨማሪም የህዝባችን የሰብዓዊ መብት መከበር ጉዳይ ለድርድር ጉዳይ ስለማይሆን የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና የህዝብ እምባ ተቋማትን አቅም ይበልጥ ለማጠናከር ወሳኝ ይሆናል፡፡

የዲሞክራሲ ልምምድና የህግ የበላይነት ማስከበር ሳይጋጩ ሁለቱንም በሚዛን ለመተግበር እና አንዱን ሳይደፈጠት ሌላውን ማስከበር የምንችልበት ሁኔታ ለመፍጠር በትኩረት እንደሚሰራም ገልጸዋል፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል

መስከረም 25 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *