አቶ ልደቱ አያሌው በ100 ሺህ ብር ዋስ እንዲፈቱ ያስተላለፈው ትዕዛዝ እንዲፈጸም የኦሮሚያ ክልል ተዘዋዋሪ ችሎት ትዕዛዝ አስተላለፈ።

በኦሮሚያ ተዘዋዋሪ ችሎት ዛሬ ረፋድ የቀረቡት አቶ ልደቱ አያሌው የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ውሳኔ አስተላልፏል።

የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ ልደቱ አያሌው በ100 ሺህ ብር ዋስ እንዲፈቱ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።

ይሁንና በዚህ ውሳኔ ላይ አቃቢ ህግ ይግባኝ በመጠየቁ ምክንያት እስካሁን ድረስ ከእስር ያልተፈቱት አቶ ልደቱ ዛሬ በኦሮሚያ ክልል ተዘዋዋሪ ችሎት ቀርበዋል።

ፍርድ ቤቱም ከዚህ በፊት በ100 ሺህ በር ዋስ እንዲፈቱ የተላለፈው ትዕዛዝ እንዲፈጸም ማጽናቱን የኢዴፓ ሊቀመንበር አቶ አዳነ ታደሰ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

አቃቢ ህግ የአቶ ልደቱ አያሌው በዋስ ቢወጡ ማስረጃ ያጠፉብኛል በማለት ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ ቢያቀርብም ፍርድ ቤቱ የአቶ ልደቱ አያሌው የፖለቲካ ስብዕናቸው ይሄንን አያመለክትም በሚል ከዚህ በፊት የተወሰነው ውስኔ እንዲከበር ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
መስከረም 26 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *