የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በጣና ሀይቅና በርብ ወንዝ መሙላት ምክንያት ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎች 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገች፡፡

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የባህርዳር-ደሴ ሀገረ-ስብከት በጣና ውሀ መሙላት ምክንያት ለተጎዱ ከ2 ሺህ 600 በላይ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ማድረጓን ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከችው መግለጫ አስታውቃለች፡፡

በዚህ የጎርፍ መጥለቅለቅ ምክንያት በ6 ቀበሌዎች በከፍተኛ ሁኔታ በጎርፍ ለተጎዱ ነዋሪዎች ነው ድጋፍ የተደረገው፡፡

ድጋፉም ለ1 ሺህ 150 አርሶ አደሮች 287 ሄክታር መሬትን ዳግም ወደ ሰብል ለመመለስ የሚያስችል ዘር የሚዉል ገንዘብ ለ200 ሰዎች ምርጥ ዘር በዓይነት የተከፋፈለ ሲሆን፣ ለ900 አባወራዎችና እማወራዎች የምግብ ድጋፍ በተጨማሪም ለ360 ሴቶች የንጽሕና መጠበቂያዎችን ድጋፍ መደረጉን ነው የተገለጸው፡፡

በአጠቃላይ በ6ቱ ቀበሌዎች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚኖሩና ለአደጋዉ በዋናነት ተጠቂ ለሆኑት ለ2 ሺህ 610 ነዋሪዎች ድጋፍ ተደርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን የባህርዳር-ደሴ ሀገረ-ስብከት አቡነ ልሳነ ክርስቶስ ማቴዎስ ድጋፉ ከቤተክርስቲያኗ ልጆች እና ረጅዎች ከሲ አር ኤስ እንዲሁም ከእማሆይ ተሬዛ ማህበር የተገኘ መሆኑን አስታዉቀዋል፡፡

በጣና ሀይቅ ውሀ መሙላት ምክንያት 3 ሺህ 750 ሄክታር በሰብል የተሸፈነ ማሳ በዉሃ በመጥለቅለቁ ሙሉ በሙሉ ከምርት ዉጭ የሆነ ሲሆን ዳግም ወደ ሰብል ለመመለስ 4 ሺህ 290 ኩንታል ዘር የሚፈልጉ አርሶ አደሮች ድጋፍ እየጠየቁ ይገኛሉ፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በደረሰ አማረ
መስከረም 26 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *