ትራንፕ ወደ ቢሯቸው ተመልሰዋል

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኮቪድ 19 መያዛቸው ከተነገረ ከሳምንት ባነሰ ጊዜ ወደ ነጩ ቤተመንግስት ተመልሰው ስራቸውን ጀምረዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ከኮቪድ ምልክቶች ነጻ ከሆኑ 24 ሰዓታት ማለፋቸውን እና የሰውነት ሙቀታቸው ከተስተካከለ ከአራት ቀናት በላይ ማለፋቸውን ሃኪማቸው ሾን ኮንሌይ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ረቡዕ ለት ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክት ‹‹ጥሩ ›› ስሜት እንደሚሰማቸው እና የፈጣሪ ቸርነት እንዳልተለያቸው ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል ብሏል ቢቢሲ፡፡

ሁሉም አሜሪካውያን እርሳቸው የተሰጣቸውን ህክምና ማግኘት እንዲችሉ ፍላጎታቸው መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ትራምፕ አያይዘውም በሪጄኔሮን ፋርማሲቲካል የሚመረተውን መድሃኒት በነጻ እንደሚያቀርቡ ቃል ገብተዋል፡፡

እርሳቸው ባለፈው ሳምንት የወሰዱት በሙከራ ላይ አንቲቦዲ ውህድ የማዳን አቅሙ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ዶዝ በቅርቡ እንደሚቀርብም ተናግረዋል፡፡

‹‹ በቫይረሱ ተያዝኩ፡፡ ስለዚህ መድሃኒት ሰማሁ፡፡ ልውሰደው አልኳቸው፡፡

 ውጤቱም ድንቅ ሆነ ›.› ካሉ በኋላ አያይዘውም መድሃኒቱ ጥቅም ላይ የሚውልበት ፈቃድ እንዲያገኝ ጥረት እንደሚያደርጉም ተናግረዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
መስከረም 28 ቀን 2013

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *