ፈረንሳይ ተጨማሪ አራት ከተሞች ላይ ባርና ሬስቶራንቶች እንዲዘጉ ወሰነች፡፡

በሃገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት መስፋፋቱን ተከትሎ ካፌና ሬስቶራንቶች እንዲዘጉ እየተደረጉ ነዉ፡፡

አገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች መስፋፋትን ተከትሎ በፓሪስ የሚገኙ ባር እና ሬስቶራንቶች ለቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታት እንዲዘጉ አደርጋ ነበር።

የተጠቂዎች ቁጥር መስፋፋቱን ተከትሎ ተጨማሪ አራት ከተሞች በተለይም ሊዮን፣ ሊሌ፣ ግሪኖብልና ቅዱስ ኢቲኔ በተባሉ አራት ከተሞች ካፌና ሬስቶራንቶች እንዲዘጉ ተወስኗል፡፡

የሃገሪቱ የጤና ሚንስትር ኦሊቨር ቨራን እንዳሉት በየእለቱ በኮሮና ቫይረስ የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን አንስተዉ በቀን እስከ 18 ሽህ የሚሆኑ ሰዎች በኮረና ቫይረስ እየተጠቁ መሆኑን ለፍራንስ 24 ተናግረዋል፡፡

የፈረንሳይ ወቅታዊ ሁኔታም በየቀኑ ከፍተኛ የተጠቂዎች ቁጥር እያስመነዘገቡ ለሚገኙት ለአዉሮፓ ሀገራት በተለይም ኔዘርላንድ፣ፖላንድና ዩክሬንን ለመሳሰሉ ሀገራት ትልቅ የማንቂያ ደወል መሆኑም ተነግሯል፡፡

በሙሉቀን አሰፋ
መስከረም 29 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *