ሚድሮክ ኩባንያ በ350 ሚሊዮን ብር አዲስ ሱፐርማርኮቶችን ሊገነባ መሆኑን አስታወቀ።

የኩባንያው ስራ አስኪያጅ አቶ ጀማል አህመድ እንዳስታወቁት ሚድሮክ ኢንቨስትመንት በአዲስ አበባ የተለያዩ ቦታዎች የኩዊንስ ሱፐር ማርኬት እንከፍታለን ብለዋል።

ለዚህ ስራም 350 ሚሊዮን ብር በጀት መያዙን የተናገሩት አቶ ጀማል ሱፐርማርኬቶቹ በቀጣዮቹ ሶስት ወራት ውስጥ ተጠናቀው ወደ ስራ እንደሚገቡም ተናግረዋል።

ሱፐር ማርኬቶቹ የሚገነቡት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ኩባንያዎች ቀድሞ ይጠቀምባቸው በነበሩ ቦታዎች ላይ እንደሆነም አቶ ጀማል ገልጸዋል።

ዳሸን ባንክ ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ኩባንያ ከሆኑት ኩዊንስ ሱፐርማርኬት እና ሆም ዲፖ ጋር በመቀናጀት ደንበኞች በዲጅታል የሚገበያዩበት የስጦታ ካርድን ዛሬ አስመርቋል።

በኢትዮጵያ በሱፐር ማርኬቶች የሚደረጉ ግብይቶች በየጊዜው እየጨመረ ሲሆን በኩዊንስ ሱፐር ማርኬት ብቻ ባሳለፍነው ሰኔ 53 ሺህ ሰዎች የተገበያዩ ሲሆን ይህ አሀዝ በሶስት ወራት ውስጥ ቁጥሩ ወደ 270 ሺህ ከፍ ማለቱ በምረቃው ወቅት ተገልጿል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሳሙኤል አባተ
መስከረም 30 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *