በብሮድካስት ባለስልጣን የህግና ማስታወቂያ ተወካይ ዳይሬክተር ዮናስ ፋንታዬ በኢትዮጵያ ከሚገኙ የመገናኛ ብዙሀን አራት መገናኛ ብዙሀን ላይ የገንዘብ ቅጣት እንደተላለፈባቸው ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
ይሁንና ዳይሬክተሩ ቅጣቱ የተላለፈባቸውን መገናኛ ብዙሃን ስም ዝርዝር ከመናገር ተቆጥበዋል።
ቅጣቱ የተላለፈባቸው ጥራቱን ያልጠበቀ ምርት ማስታወቂያ በመልቀቃቸው እንደሆነ ተጠቁሟል። በዚህም ኃላፊነታቸውን ተወጥተው ባለመገኘታቸው በሚል በማስታወቂያ አዋጁ መሰረት ከ10 እስከ 23 ሚሊዮን ብር እንዲቀጡ ተደርጓል፡፡
በተመሳሳይም ማስታወቂያውን በግድየለሽነት በመስራት ለመገናኛ ብዙሀኑ ሰጥተዋል የተባሉት የማስታወቂያ ድርጅቶችም ላይ ቅጣት እንደተፈጸመባቸው ተገልጿል።
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8
በመቅደላዊት ደረጀ
ጥቅምት 4 ቀን 2013 ዓ.ም











