በኦሮሚያ ክልል ባለፉት አምስት ቀናት በደረሰ የትራፊክ አደጋ 6 ሰዎች ሲሞቱ በሁለት ሰው ላይ ደግሞ ከባድ አካል ጉዳት ደርሷል።

የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ የትራፊክ ደህንነትና ቁጥጥር ክፍል ባለሙያ ሳጅን የባሌወርቅ ደጀኔ ለጣቢያችን እንደተናገሩት በሳምንቱ 6የሞት 2 ከባድ እና 10የንብረት አደጋ መከሰታቸውን ነግረውናል።

የሞት አደጋው በምስራቅ ሸዋ ቦሴት ወረዳ፡ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ሰንዳፋ በኬ ከተማ፡ ሰበታ ወረዳ፡ ቡኖ በደሌ በደሌ ከተማ እና በጅማ ከተማ የደረሱ ናቸው።

መንስኤውም የጥንቃቄ ጉድለትና ለእግረኛ ቅድሚያ ባለመስጠት መሆኑን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል።

በአደጋው ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ከ25 እስከ 50 የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው።

ሰሜን ሸዋ ደብረ ሊባኖስ ወረዳና ኦሮሚያ ዞን ሰንዳፋ በኬ ከተማ ከባድ አደጋ ደርሷል።

በአጠቃላይ በሳምንቱ ከ200 ሚሊየን በላይ የንብረት ውድመት መድረሱን ሳጅን የባሌወርቅ ደጀኔ ነግረውናል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በመቅደላዊት ደረጀ
ጥቅምት 6 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.