በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ከ600 ሚሊዮን በላይ ህፃናት ተገቢውን እርዳታ ማግኘት አልቻሉም፡፡

የህፃናት አድን ድርጅት በዓለማችን መካከለኛና ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ከሚኖሩ ቤተሰቦች የተገኙ ወደ 594 ሚሊዮን የሚጠጉ ህፃናት ኮቪድ 19ን ለመቋቋም የሚያስፈልጋቸውን የገንዘብ እርዳታ ከሃገሮቻችው መንግስታት እንዳላገኙ አስታውቋል፡፡

የህፃናት አድን ድርጅት የዓለም ባንክና የተባበሩት መንግስታት ጥናት እንደሚያሳየው ከሆነ 68 ያህል በሚሆኑ የዝቅተኛና መካከለኛ የገቢ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሃገራት ውስጥ ያሉ ቤተሰቦች ለህፃናት ልጆቻቸው ቀለብና መስረታዊ ፍላጎቶችን ማሟላት እንዳልቻሉ ነው ያስታወቀው፡፡

በዚህም ምክንያት ከ594 ሚሊዮን በላይ ህፃናት ተጎጂዎች ሆነዋል፡፡

የህፃናት አድን ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንገር አሺንግ እንደተናገሩት ብዙሃንን ከስራ ገበታቸው ያፈናቀለው ኮቪድ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህፃናትንም የጤና አቅርቦት፤ ትምህርት፤ ምግብ እንዲሁም መጠለያን ሊያሳጣ ይችላል ብለዋል፡፡

ከወረርሽኙ በፊት ወደ 1 ቢሊዮን ያህል ልጆች ያለ በቂ የጤና፤ የትምህርት፤ የመጠለያ እና ንፁህ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት በድህነት የኑሮ ደረጃ ላይ እንዲኖሩ አስገድዷቸው የነበረ ሲሆን፡
ኮቪድ-19 ከመጣ ወዲህ ይህ ቁጥር በ150 ሚሊዮን ጨምሮ 1.2 ቢሊዮን መደረሱን ነው ስራ አስፈጻሚው የተናገሩት፡፡

ከኮቪድ -19 ወረርሽኝ የተማርነው ቁልፍ ነገር ቢኖር ሰዎች እንዲሁም ማህበረሰቡ ይህንን አስቸጋሪ ጊዜ ለመሻገር ጠንካራ የፋይናንስ ድጋፍ እንደሚሹ ነው፡፡

መንግስታት ከገቢያቸው ላይ አንድ በመቶ ያህል ቀንሰው ቢያበረክቱ ድህነትን 20 በመቶ መቀነስ ብቻ ሳይሆን በዛውም ልክ የህፃናትንም ተስፋ ብሩህ ያደርጋሉ ሲሉ ተናግረዋል ኢንገር አሺንግ ፡፡

ከኮቪድ -19 ወረርሽኝ በፊት 35 በመቶ የአለም ህፃናት ማህበራዊ ድጋፎች ይደረግላቸው ነበር፡፡

ከዚህም ውስጥ 28 በመቶውን የእስያ 16 በመቶውን ደግሞ የአፍሪካ ህፃናት እንደሚይዙ ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት፡፡

በሔኖክ ወገብርኤል
ጥቅምት 6 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *