በደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ 54 ሺህ ዜጋ የረሀብ አደጋ ተጋርጦበታል ተባለ።

ከመስከረም 16 ጀምሮ በወረዳው የገባው የአንበጣ ወረርሽኝ በወረዳው ከሚኖረው ከ130 እስከ 140 ሺህ የሚጠጋ ነዋሪ 50 ሺህ የሚያህለውን የወረዳውን ነዋሪ የረሀብ አደጋ ጋርጦበታል።

በወረዳው 9 ሺህ ሄክታር የሚያህል የማሽላ ማሳ ሙሉ ለሙሉ ወድሟል።

በወረዳው የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሳዳም ሽምልስ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት ካሉት 20 የገጠርና 3 የከተማ ቀበሌዎች የ 12 ቀበሌ የማሽላ ሰብል ሙሉ ለሙሉ ወድሟል።

2 ቀበሌዎች ስጋት ላይ ናቸውም ብለዋል።

ገብሬው ያለበት ሁኔታ እጅግ አሳዛኝ ነው፣ ውሎ አድሮ የሁላችንንም ቤት ማንኳኳቱ ስለማይቀር ፣ለገበሬው ከሁሉም ኢትዮጵያዊ፣ አስቸኳይ፣ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ያስፈልገዋል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል አቶ ጂብሪል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ አስራት
ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.