በኢትዮጵያ የተከሰተው በረሃ አንበጣ መንጋ ታርሶ በነበረ 420 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ጉዳት ማድረሱን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አሳወቁ፡፡

ዛሬ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ከ4 ሚሊየን ከታረሰ መሬት ውስጥ 420 ሺህ ሄክታር መሬት ብቻ ነው በአንበጣ ጉዳት የደረሰበት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዳቱ ሀገሪቱ በዘንድሮ አመት ልታመርት ያቀደችውን 35 ሚሊየን ኮንታል እህልን የሚሳጣ እንዳልሆነ አብራርተዋል፡፡

አንበጣው ሊያደርስ የሚችለው ጉዳት ሲጠና ከ25 በመቶ ያልበለጠ እንደሆነም ተናግረዋል።
በከፊል ኦሮሚያ ትግራይ አፋር አማራ ባሉ 240 ወረዳዎች ውስጥ በ94ቱ ባሉ 775 ቀበሌዎች ውስጥ የአንበጣ መንጋ ተከስቷል ብለዋል፡፡

በነዚህ ቀበሌዎችም ከታረሰው 4 ሚሊየን ሄክታር መሬት ውስጥ በ420 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ መንጋው ጉዳት ማድረሱን ተናግረዋል፡፡

መንግስትም ጉዳቱን ለመቀነስ የአውሮፕላን ርጭቱን አጠናክሮ ቀጥሏል አስፈላጊ የሚባለውንም ድጋፍ ያደርጋል ሲሉ አብራርተዋል፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *