በኦሮሚያ ክልል ባለፉት ሁለት ቀናት 2 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

አደጋው የደረሰው በምስራቅ ሀረርጌ ኮምቦልቻ ወረዳ ሲሆን ሁለት አሽከርካሪዎች ተጋጭተው የአንዱ አሽከርካሪ ህይወት ወዲያውኑ ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ ጥናት ግንባታ ዲቪዥን ባለሙያ ሳጅን የባሌወርቅ ደጀኔ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

ሌላኛው ደግሞ በምስራቅ አርሲ ሮቤ ሮቤ ከተማ ሚኒባስ ታክሲ አንድ እግረኛውን ገጭቶ ያደረሰው ጉዳት ነው፡፡

መንስኤውም ለእግረኛ ቅድሚያ ባለመስጠት እንደሆነ ሰምተናል፡፡

ሳጅን የባሌወርቅ ደጀኔ እንደነገሩን ከተመሳሳይ ቀናት ጋር ሲተያይ ያለፉት ሁለት ቀናት አደጋ ቀንሷል ብለዋል፡፡

በመቅደላዊት ደረጀ
ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *