ኤል ጂ ኤሌክትሮኒክስ ከወርልድ ቱጌዘር ጋር በመተባበር ለኮርያ ዘማች ኢትዮጵያዊያን ከስምንት መቶ ሺህ ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ፡፡

የኮርያው ኤል ጂ ኤሌክትሮኒክስ በኮርያ ጦርነት ለተሳተፉ 134 ኢትዮጵያዊያን ለእያንዳንዳቸው 6 ሺህ ብር ድጋፍ አድርጓል።

ድርጅቱ ከገንዘብ በተጨማሪም በሽታ የመቋቋም አቅም የሚጨምር ቫይታሚንም ድጋፍ አድርጓል፡፡

በኢትዮጵያ የወርልድ ቱጌዘር ሀላፊ ሚስተር ፓርክ ዩንግኩ እንደተናገሩት ለኮርያ ነጻነት ለታገሉ አርበኞች ትልቅ ክብር እንዳለቸው ተናግረው ድርጅታቸው ለኮርያ ዘማቾች የተለያዩ ድጋፎችን እንዳደረገ እንደሚገኝ እና ወደ ፊትም ድጋፉ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የኤል ጂ ሰራተኞች ማህበርም ለኮርያ ዘማቾች የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ቁሳቁሶችን እንዳደረገ ነው የተነገረው፡፡

ወርልድ ቱጌዘር እና ኤልጂ ኤሌክትሮኒክስ በኢትዮጵያ ለሚገኙ በኮርያ ጦርነት ለተሳተፉ አርበኞች ተጠቃሚ ያደረጉ ስራዎችን እየሰሩ የሚገኙ የኮርያ ድርጅቶች ናቸው፡፡


የኮርያ ጦርነት ከዛሬ 70 አመት በፊት የተደረገ ጦርነት ሲሆን በጦርነቱ ከ6 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ዘማቾች ተሳትፈዋል፡፡

በጦርነቱም ከ120 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያ ዘማቾች ህይወታቸው እንዳለፈ ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት፡፡

የኮርያ መንግስትም በጦርነቱ ለተሳተፉ ኢትዮጵያዊያን ዘማቾች እና የዘማቾቹ ልጆች በተለያዩ ጊዜያት ድጋፎችን እያደረገላቸው ይገኛል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *