ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ ማስክ ሳያደርግ ወደ ስራ እንዳይገባና አገልግሎት እንዳይሰጥ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳሰበ።

ኢንስቲትዩቱ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመሆን አስካሁን በተሰሩ የኮሮና ቫይረስ መካላከል ስራዎች እና በቀጣይ እቅዶች ዙሪያ በአዲስ አበባ እየመከሩ ነው።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኤባ አባተ በዚህ ጊዜ እንዳሉት እስካሁን በኢትዮጵያ በቫይረሱ ከሚያዙት 57 በመቶ የሚሆኑት እድሜያቸው ከ15-34 ሲሆን ከሟቾች ውስጥ ደግሞ 51 ነጥብ 9 በመቶ የሚሆኑት ዕድሜያቸው ከ60 ዓመት በላይ ነው።

በቫይረሱ የሞት ምጣኔ በኢትዮጵያ 1.52 በመቶ ፣ በአፍሪካ 2.4 በመቶ ፣ በዓለም ደግሞ 2.8 በመቶ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም ህብረተሰቡ ሳይሰላች ቫይረሱን ለመከላከል የሚሰጡ ዘዴዎችን በአግባቡ እንዲተገብር አሳስበዋል፡፡

ተቋማትም ቢሆኑ ለሰራተኞቻቸው ለኮቪድ መከላከያ የሆኑት ዘዴዎች እንዲጠቀሙ አስገዳጅ ማድረግ አለባቸው ብለዋል፡፡

የትምህርት ቤቶች አከፋፈት ጠንካራ ዝግጅት የተደረገበት መሆኑን ገልጸዉ፤ ከተከፈተም በኋላ ከጤና ተቋማት ጋር አብሮ ይሰራል ብለዋል።

ዶክተር ኤባ ትምህርት ቤት ለመክፈት መወሳናችን ትክክለኛው ሰአት ነውም ብለዋል።

በትምህርት ቤቶች አከፋፈት ጉዳይ ከህብረተሰቡ የሚነሳው ስጋት ትክክል ቢሆንም ነገር ግን አለመከፈቱ ከሚያደርሰው ችግር አንጻር መከፈቱ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል ብለዋል፡፡

እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስም ሁሉም ትምህርት ቤቶች ክፍት እንዲሆኑ ታስቧል ብለዋል፡፡

ከአስከሬን ምርመራ ጋር በተያያዘ ደግሞ ከዚህ በፊት ይደረግ የነበረው የአስከሬን ምርመራ ኢትዮጵያ ምን ያህል ኮሮናን ለመከላከል ቁርጠኛ መሆኗን ያሳየ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል።

አስከሬን ስንመረምር ለሌላ መረጃ አቅጣጫ ይሰጠናል በሚል ታሳቢ ተደርጎ ነበር ያሉት ሃላፊዉ፤አሁን ላይ የአስከሬን ምርመራው እንደቆመም ታዉቋል፡፡

በመቅደላዊት ደረጀ
ጥቅምት 10 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *