ከብሄራዊ ባንክ መረጃ ካልተነገረ በስተቀር አሮጌዎቹ የብር ኖቶች ስራ ላይ መዋላቸውን ይቀጥላሉ ተባለ።

የብሔራዊ ባንክ ዋና ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው።
በዚህ ጊዜ እንዳሉት ባንኮች አዲሱን ብር ሲቀይሩ አሮጌውን ብር ቢሰጡም ምንም ችግር የለውም ህብረተሰቡ ክርክር ውስጥ መግባት የለበትም ብለዋል።

ባንኮች እጥረት ካልገጠማቸው በቀር ባንኮችም አሮጌውን ብር እንዳይሰጡ ከብሔራዊ ባንኮች ለሁሉም ባንኮች መመሪያ ተላልፏል ብለዋል ዶክተር ይናገር።

ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ 105 ቢሊየን አዲስ ቁጠባ ተመዝግቧል ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር 6 እጥፍ ነው ብለዋል።

ለዚህም ከባንክ የሚወጣን ጥሬ ገንዘብ መገደብ እንደ ምክንያት ያነሱት ከአዲሱ የገንዘብ ኖት ቅያሪ ጋር በተያያዘ ሲሆን እስካሁንም 37 ቢሊዮን ብር ወደ ባንክ ገቢ መደረጉን ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈ ባለፉት ሶስት ወራት 33 ነጥብ 46 ቢሊየን ብር ከግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ መገኘቱንም ዶክተር ይናገር ተናግረዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በመቅደላዊት ደረጀ
ጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *