በኢትዮጵያ 12 ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኩባንያዎች የኮሚኒኬሽን ኦፕሬተር ፍቃድ ለመውሰድ ፍላጎት ማሳየታቸው ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ኮምንኬሽን ባለስልጣን እንዳስታወቀው 12 ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኩባንያዎች የኮሚኒኬሽን ኦፕሬተር ስራ ዘረፍ ለመሰማራት ፍላጎት አሳይተዋል።

ፍላጎት ካሳዩ ዓለም አቀፍ የቴሌኮምንኬሽን ኩባንያዎች መካከልም “ዓለምአቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ” በሚል ጥምረት ቮዳፎን፣ ቮዳኮም እና ሳፋሪኮም በአንድ ላይ ኢቲሳላት ፣አክሲያን ፣ኤምቲኤን ፣ኦሬንጅ ፣ሳውዲ ቴሌኮም ኩባንያ ፣ ቴሌኮም ደቡብ አፍሪካ ፣ ሊኪውድ ቴሌኮም እና ስኔይል ሞባይል ተጠቃሽ ናቸው።

እንዲሁም ሌሎች ሁለት የቴሌኮም ኦፕሬተር ያልሆኑ ድርጀቶችም በኢትዮጵያ የቴሌኮም ስራዎች ለመሳተፍ ያመለከቱ ሲሆን ካንዱ አለምአቀፍ ቴሌኮሙኒኬሽን እና ኤሌክትሮሜካ አለምአቀፍ ፕሮጀክቶች ናቸው።

ከነዚህ በተጨማሪም የጂቡቲ ኢንቬስተሮች ሸርክና ቡድን ለሚሰጡት ፍቃዶችም የግብይት አማካሪ የመቅጠርና ወደ ስራ የማስገባት ስራ መከናወኑን ባለስልጣኑ ተገልጿል።

በመቅደላዊት ደረጀ
ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *