በደቡብ ክልል በጉራ ፈርዳ ወረዳ ከደረሰው ጥቃት ጋር በተያያዘ በህግ ቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች 54 ደረሰ።

በአከባቢዎች ታጣቂ ናቸው የተባሉ ሰዎች ባደረሱት ጥቃት 31 ሰዎች መገደላቸው የሚታወስ ነው፡፡

እንዲሁም በሶስት ቀበሌዎች ጥቃቱን በመፍራት ከ2 ሺህ 635 በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን የክልሉ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲ ለኤትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

አቶ አለማየሁ እንዳሉት በአከባቢው ላይ የተፈጠረውን ችግር መነሻ ነው የተባለው አንድ ግለሰብ በአሰቃቂ ሆኔታ ተገድሉ ተገኘ መባሉ መሆኑን ያነሳሉ፡፡

ይሆን እንጂ ችግሩን በሰከነ መንገድ ከመፍታት ይልቅ የፖለቲካ አመራሮች ከወረዳ እስከ ቀበሌ ያሉ የስራ ሀላፊዎች ጭምር በማቀጣጠል ግጭቱ እንዲባባስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ደርሰንበታል ነው ያሉት፡፡

የደረሰው ጥፋት እጅግ አጸያፊ ስለመሆኑ የሚናገሩት ሀላፊው በጉዳዩ ላይ ተሳትፈዋል የተባሉ ከወረዳ እስከ ቀበሌ ድረስ ያሉ የፖለቲካ አመራሮች እና ሌሉች ሰዎች ተሳትፏቸውን የተመለከተ ምርመራ እያደረግን ነው ፡፡በጥፋታቸው ልክም ይጠየቃሉ ብለዋል፡፡

በችግሩ ሰብብ ከሶስት ወረዳዎች የተፈናቀሉ 2ሺህ 635 ነዋሪዎች አሰቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ መሰጠቱን አንስተው ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ግን አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን ተጨማሪ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ማሰማራት ላይ እየተሰራ መሆኑን ነግረውናል አቶ አለማየሁ፡፡
ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *