የኢትዮ ጅቡቲ መንገድ ካልተስተካከለ ነዳጅ ለማቅረብ እንደሚቸገር የኢትዮጵያ የፈሳሽ ጭነት ማጓጓዣ ባለንብረቶች ማህበር አስታወቀ።

የማህበሩ ሰብሳቢ አቶ ጸጋ አሳመረ ከማህበሩ ስራዎች ጋር በተያያዙ በርካታ ጉዳዮች ዙሪያ በአዲስ አበባ መግለጫ ሰጥተዋል።

ሰብሳቢው በዚህ ጊዜ እንዳሉት መንግስት ለነዳጅ ዘርፍ የሰጠው ትኩረት አነስተኛ መሆኑን አስታውቋል።

የነዳጅ ዘርፉን ብቻ የሚመራ ባለሙያ የለም፣ በዚህ በኩል የሚሰሩ ባለሙያዎች ከሌሎች ስራዎች ጋር ደርበው ይሰሩታል እንጂ ራሱን የቻለ ባለሙያ የለም ተብሏል።

ይሄ ሁሉ መነሻ የመንግስት ለዘርፉ የሰጠው ትኩረት ማነስ ነው ተብሏል
የነዳጅ አቅርቦቱ ችግር ውስጥ ገብቷል ብለን መንግስት ችግሩን እንዲፈታ በተደጋጋሚ ብናነሳም ምላሽ አላገኘንም ቀርቦም ምን እናድርግ ብሎ ያዋራን አካል የለም ብለዋል።

የጅቡቲ መንገድ ዋነኛ ችግራችን ነው ያሉት አቶ ጸጋ መንገዱ ካልተስተካከለ አሁንም ቢሆን ነዳጅ ለማቅረብ እንቸገራለን ብለዋል።

የነዳጅ ጉዳይ ከፖለቲካ መውጣት አለበት ያለው ማህበሩ መንግስት ይሄንን ችግር እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም መፍትሄ ካልሰጠ ስራችንን እናቆማለን ብሏል።

በመቅደላዊት ደረጀ
ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *