ግብፅ ጥላው የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተጨማሪ 3 ወራት አራዘመች።

የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ ከትናንት ጀምሮ በሀገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለተጨማሪ ሶስት ወራት ማራዘሙን አንድ የመንግስት ቴሌቪዥን ዘግቧል ፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወታደራዊ እና ፖሊሶች ሽብርተኝነትን እና ተቃውሞ ለመቀስቀስ የሚያስቡት ላይ አስፋላጊ ናቸው የሚሏቸውን እርምጃዎች እንዲወስዱ እንዲሁም ግለሰቦችን እና የመንግስት እና የግል ንብረቶችን እንዲጠብቁ የሚያስችል መብት ይሰጣል ሲል ሚዲል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡

ይህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአልሲሲ መንግስት በሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎችን ለማሰር እና ለማፈን እንደ ማመካኛ ጥቅም ላይ ሲል አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹች ይናገራሉ፡፡

ሂውማን ራይትስ ወች (HRW) በግብፅ የፖለቲካ እስረኞች ቁጥርን ቢያንስ 60 ሺህ ያደርሳቸዋል፡፡

በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡት ፕሬዝዳንት ሞሃመድ ሙርሲን በ2013 ወታደራዊ መፈንቅለ ከስልጣን ያባረሩት አልሲሲሰ ከያኔ ጊዜ ጀምሮ በተቃዋሚዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክረዋል ፣ ተቃውሞዎችን አግደዋል እንዲሁም ወሳኝ የሆኑ ድምፆችን ለማፈን በመገናኛ ብዙሃን ላይም ቁጥጥራቸውን ጨምረዋል ነው የሚባለው ፡፡

የሙርሲ የሙስሊም ወንድማማቾች ቡድን አሸባሪ ድርጅት ብሎ በግብጽ ተፈርጇል፡፡

ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ብዙ የድርጅቱ አባላት ለእስር ተዳርገዋል ወይም በኃይል ጠፍተዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ጥቅምት 18 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *