ነገ ሌሊት ውጤቱ የሚታወቀው የአሜሪካ ፕሬዘዳንቲዊ ምርጫ በቅድመ የህዝብ አስተያየት ጆ ባይደን እየመሩ ነው፡፡

ድምፅ ሰብሳቢ ድርጅቶች የትኛውን ዕጩ ነው የምትመርጡት እያሉ ከአሜሪካውያን የሚሰበስቡትን ድምፅ ይፋ አድርገዋል፡፡

በዚህም ጆ ባይደን 52 ከመቶ ያገኙ ሲሆን ዶናልድ ትራምፕ ደግሞ 48 ከመቶ አግኝተዋል፡፡

በቢቢሲ የህዝብ አስተያየትም ጆ ባይደን ከፍተኛ የማሸነፍ ግምት እንዳለቸው ነው የጠቆመው፡፡

ቢቢሲ ከፍተኛ ድምጽ ይሰጥባቸዋል ብሎ ከህዝቡ ድምጽ ከሰበሰበባቸው ከ14 የአሜሪካ ግዛቶች መካከል በአስራ ሁለቱ ጆ ባይደን ያሸነፉ ሲሆን ዶናልድ ትራምፕ በሁለቱ ግዛቶች ብቻ ነው ማሸነፍ የቻለው ብሏል፡፡

ከነዚህ ግዛቶች መካከል ሚቺጋን ሚኒሶታ ቴክሳስ ቨርጂኒያ ኔቫዳ ሰሜን ካሮሊና እና ሌሎችም ግዛቶች ይገኙበታል፡፡

ትራምፕ በመጨረሻው ቀን በሚቺጋን፣ በኖርዝ ካሮላይና፣ በጆርጂያ እና በፍሎሪዳ የምረጡኝ ዘመቻዎችን አድርገዋል፡፡

በዋሽንግተን ባደረጉት ንግግርም በአስተዳደር ዘመናቸው የሃገሪቱ ኢኮኖሚ ከየትኛውም ጊዜ በተሸለ እደገት አሳይቷል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ከ1945 በፊት በአሜሪካ ታሪክ ፈራንክሊን ሮዝቨልት ለሶስት ተከታታይ የምርጫ ዘመናት አሜሪካን የመሩ ፕሬዝዳንት ነበሩ፡፡

ከሮስቨልት ወዲህ ግን የአሜሪካ ህገመንግስት ላይ አንድ ፕሬዝዳንት ለሁለት ተከታታይ የምርጫ ዘመናት ቢቻ እንዲመራ በ1945 ህግ ሆኖ ተደንግጓል፡፡

በሀገሪቱ ታሪክ ውስጥ ለአንድ የስልጣን ዘመን ብቻ የመሩ አምስት ፕሬዝዳንቶች ናቸው እነሱም ዊሊያም ሐዋርድ፣ሔርበርት ሁቨር፣ ጅሚ ካርተር፣ትልቁ ቡሽ እና ኒክሰን ናቸው፡፡

ባሁኑ ሰአት ከጆ ባይደን ጋር እየተፎካከሩ የሚገኙት ዶናልድ ትራምፕ በብዙዎች ዘንድ የነዚህን ፈለግ ሊከተሉ እንደሚችሉ እየተናገሩ ነው የሚገኙት፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.